የሲቪል ማኅበራት መረጃ ማዕከል በሐምሌ 2012 በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት በቦርድ የሚመራ ሲቪል ማኅበረሰብ ሆኖ ተመዘገበ ፡፡

የሲቪል ማኅበራት መረጃ ማዕከል ዋና ዓላማ አዲስ እና ነባር ሲቪል ማኅበራትን መለየትና መደገፍ ሲሆን የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ዘርፍን መልሶ በመገንባት ያግዛል ፡፡

የሲቪል ማኅበራት መረጃ ማዕከል በኢትዮጵያ ውስጥ ንቁ የሲቪል ማህበረሰብ ተሳታፊዎች በምርምር ፣ በቅስቀሳ እና በመረጃ ስርጭት ዙሪያ ለማጎልበት ይሰራል፡፡

የሲቪል ማኅበራት መረጃ ማዕከል በሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እና በአስተዳደር ጉዳዮች ላይ በተሰማሩ የሲቪል ማህበረሰብ ተሳታፊዎች ልዩ ትኩረት ይሰጣል ፡፡

የስልጠና እና የግብዓት ማዕከል የሲቪል ማህበራትን ዘርፍን መልሶ ለመገንባት እና ትብብርን ለማበልፀግ አስፈላጊ እገዛ ያቀርባል ፣ በተጨማሪም ተመሳሳይ አመለካከት ባላቸው የሲቪል ማህበራት መሪዎች መካከል የግንኙነት መድረክ የዘጋጃል ፡፡

አገልግሎት


የድጋፍ አግልግሎት


የሲቪል ማህበረሰብ መረጃ ማዕከል ዋና ዋና ፕሮጀክቶች መካከል ጀማሪ የሲቪል ማኅበራትን ድጋፍ መስጠትና ማጠናከር ናቸው ፡፡ለእነዚህ ጀማሪ ድርጅቶች ማዕከሉ ሁለገብ ድጋፍ ይሰጣል።

የሥራ ቦታ አቅርቦት

ተቋማችን የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶችን እና ሠራተኞቻቸውን ዘመናዊ በሆነ ከፍተኛ ፍጥነት ባለው ኢንተርኔት ፣ የመሰብሰቢያ ክፍሎች እና የሥራ ቦታዎች እናስተናግዳለን ፡፡

የስራ ማሰናዳት እገዛ

የሲቪል ማኅበራት ድርጅት አባሎችስ እንዲጠቀሙበት የስራ ሂደት ፣ የገንዘብ መመሪያዎች እና የስራ ቅፆች እናዘጋጃለን ፡፡ በተጨማሪም ማዕከሉ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ስራ መጀመራቸውን ተከትሎ የህግ (ምዝገባን ጨምሮ) ፣ የገንዘብ እና የስራ ማሰናዳት አስተዳደር እገዛ ያቀርባል።

የምርምር ድጋፍ

በሰብአዊ መብት ፣ በአስተዳድር እና በተዛማች ስራዎች ላይ የተሰማሩ ሲቪል ማህበራትን የምርምር ድጋፍ እንሰጣለን ፡፡

የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶችን ማስጀመር

እያንዳንዱ አባል ድርጅት ቢያንስ አንድ (ዎርክሾፕ ፣ ውይይት ወይም መርሐግብር ማስጀመሪያ) ዝግጅቶችን እንዲያደራጁ ድጋፍ እንሰጣለን፡፡

ስልጠና እና ሜንቶርሽፕ

ለወጣት የሲቪል ማኅበራት መሪ አባላቶችን  የስራ ዑደት አስተዳደር ፣ የስልታዊ እቅድ እና የመርሐግብር አያያዝ ላይ ስልጠና እና ሜንቶርሽፕ እንሰጣለን ፡፡

ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የስልጠና እና መረጃ ክፍለ ጊዜ


የሲቪል ማኅበራት መረጃ ማዕከል አዳዲስ ሕጎችን ፣ መመሪያዎችን ፣ የሕግ ማስታወሻዎችን ፣ ወዘተ. በተጨማሪ ከሲቪል ማኅበራት ኤጄንሲ ጋር በመተባበር ፣ ወርሃዊ የሥልጠናና የመረጃ ክፍለ ግዜዎችን በማዘጋጀት የሲቪል ማኅበረሰብ ዘርፍ አባላትን እና አጠቃላይ ሕዝቡን ወቅታዊ መረጃ ለማሳወቅ እንደ አዳዲስ መመሪያዎች ፣ ደንቦች ፣ የሕግ ማስታወሻዎች ፣ የምዝገባ እና የሪፖርት ማቅረቢያ ሳንፕሎችን አሰራሮች በተጨማሪም በአዲሱ የሲቪል ማኅበረሰብ አደረጃጀት ሕግ መሠረት የሚወጣው ተጨማሪ ሕጎችን በመከታተል ይመዘግባል፡፡

ዝግጅቶችን ይመልከቱ